የአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ ኮሪደር ሥራ ተጠናቋል።
አካባቢውን አረንጓዴ የማድረግ ጥረቱ በጉልህ ይታያል። ባለፉት ሳምንታት የምሽቱን ውበት እንዳደነቅነው ዛሬ ደግሞ የማለዳን እይታ በኮሪደር ልማታችን ተመልክተናል። ለስኬቱ በሥራው ለተሳተፉት የከተማው አስተዳደር እና በሙሉ ፈቃድ ለተሳተፉ የግሉ ሴክተር ምስጋና ይገባል።
የከተማችንን የመኪና ማቆሚያ እጥረት የሚቀርፉ የፓርኪንግ ቦታዎች ተገንብተዋል። የእግር ጉዞን የሚያበረታቱ የእግረኛ መንገዶች ተስፋፍተው ተሰርተዋል።
ይህን ባሕል መንከባከብ እና ማሳደግ ይገባል። ሁላችንም ህልው ለሆነው አዲስ መልክ ጠባቂዎች መሆን አለብን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ