የቀጨኔ መቀጠያ -ጉጃ በር መንገድ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በራስ ኃይል አጫጭር እና አቋራጭ መንገድ በመገንባት፣ የህብረተሰቡን የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄ እየመለሰ ከሚገኝባቸው ፕሮጀክቶች መካከል ከቀጨኔ መድኃኒዓለም ወደ ሽሮ ሜዳ የሚወስደው መንገድ አንዱ ነው፡፡
ቀደም ሲል በዚህ አካባቢ አማራጭ የመንገድ መሰረተ-ልማት ባለመዘርጋቱ ምክንያት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ሲፈተን ቀይቷል፡፡
በተለምዶ ቀጨኔ መቀጠያ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ወደ ሽሮ ሜዳ ቁስቋም ወይም ጉጃ በር ለመጓዝ፤ የተለያዩ እቃዎችን ተሸክሞ በእግር መጓዝ፣ አልያም ሁለትና ከዚያ በላይ የትራንስፖርት አማራጮችን መጠቀም ግድ ይል እንደነበር አይዘነጋም፡፡
በዚህም የተነሳ፤ የአዲስ አባባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለአካባቢው ነዋሪዎች የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እና ሽሮ ሜዳን ከቀጨኔ በአጭር ርቀት በመንገድ መሠረተ-ልማት ለማስተሳሰር 2 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን አቋራጭ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ገንብቶ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡
የቀጨኔ መቀጠያ -ጉጃ በር መንገድ ግንባታ ተከናውኖ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት መደረጉ፣ ለአካባቢው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት መፋጠን የጎላ ፋይዳ ያለው መሆኑን በቦታው ተገኝተን ያነጋገርናቸው የአካባቢው ወጣቶች ነግረውናል፡፡
አቶ አዲሱ የኔነህ ይባላል፤ የቀጨኔ መቀጠያ አካባቢ ነዋሪ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በአካባቢው የተሻለ መንገድ ባለመኖሩ በተለይም አቅመ ደካማ አዛውንቶች ወጥተው ለመግባት ይቸገሩ እንደነበር ያስታውሳል፡፡
ከመንገድ እጦት ባሻገርም የምሽት ጨለማና የክረምት ጭቃ ተደምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች በመንገድ አገልግለት ይቸገሩ እንደነበር ወጣት አዲሱ ጨምሮ ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን፤ ከቀጨኔ ጀምሮ እስከ ሽሮ ሜዳ ቁስቋም ድረስ የሚዘልቅ፣ ደረጃውን የጠበቀ የአስፋልት መንገድ በመገንባቱ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች የመንገድ መሰረተ-ልማት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን ወጣት አዲሱ እና ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በተለይም ይላል ወጣት አዲሱ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች የአምቡላስ እና ለሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለማግኘት ከፍተኛ ችግር ይገኝማቸው እንደነበር ጠቁሞ፤ አሁን ላይ መንገዱ ተገንብቶ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት መደረጉ የትራንስፖርት አማራጮችን ከማግኘት ከማስቻሉም ባሻገር፣ ጊዜንና ወጪን መቆጠብ እንዳስቻላቸው ወጣት አዲሱ ጨምሮ ነግሮናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369