+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከጀሞ አፍሪካ ሕንፃ ወደ ጀሞ መስታዎት የተገነባው መንገድ የአካባቢውን የትራፊክ ፍሰት እያቀላጠፈ እንደሚገኝ የመንገዱ ተጠቃሚዎች ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በራስ ኃይል እየገነባቸው ከሚገኙ መንገዶች መካከል አንዱ የሆነው የጀሞ አፍሪካ ሕንፃ -ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ መንገድ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት መደረጉ ለአካባቢው የትራፊክ ፍሰት መሳለጥ አስተዋፅዎ እያበረከተ እንደሚገኝ በቦታው ተገኝተን ያነጋገርናቸው አሽከርካሪዎችና የአካባቢዊ ነዋሪዎች ገልፀውናል፡፡

መንገዱን በየቀኑ የሚጠቀሙት የባጃጅ አሽከርካሪዋ ወ/ሮ ረሂማ ቦጋለ እንደገለፁት ቀደም ሲል መንገዱ ለአሽከሪካሪዎችና ለእግረኞች ምቹ ያልነበረ በመሆኑ በተደጋጋሚ ባጃጅ እየተበላሻ ለወጪ ይዳረጉ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ መንገዱ መሰራቱ የነበረውን ችግር ያቃለለና የትራፊክ ፍሰቱን ያሳለጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አቶ ቦጋለ ቦቴ ደግሞ የአካባቢዊ ነዋሪ ሲሆኑ መንገዱ ከመሰራቱ በፊት ክረምት ሲገባ መንገዱ በጭቃና በውሃ ይሞላ ስለነበር እግረኞች ለከፍተኛ እንግልትና ይዳረጉ እንደነበር አውስተው፤ አሁን ላይ መንገዱ መሰራቱ የመግቢያና የመውጫ ችግርን የፈታ ሆኗል ብለዋል፡፡

በአካባቢው ለአራት አመታት ተራ በማስከበር የሚተዳደሩት አቶ ኤፍሬም አበረ በበኩላቸው ቀደም ሲል መንገዱ ለእግረኞችም ሆነ ለተሸከርካሪዎች ምቹ ባለመሆኑ ነፍሰጡር እናቶች ወደ ሆስፒታል ለሚሄድ ይቸገሩ እንደነበር እና በምሽት ወቅት የመንገድ ዳር መብራት ባለመኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለስርቆት ሲዳረጉ መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡

አቶ ኤፍሬም አክለውም አሁን ላይ መንገዱ በመሰራቱ ቀደም ሲል የነበረውን ችግር የፈታ እና ከጀሞ ሚካኤል የቀለበት መንገድ መጋጠሚያ ወደ ጀሞ ትራፊክ መብራት እና አካባቢው ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ በመሆኑ የትራፊክ ፍሰቱን እያሳለጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 1 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ አሁን ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪም የእግረኛ መንገድ ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የመንገድ ፕሮጀክቱ የፊዚካል አፈፃፀሙ ከ93 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

Comments are closed.