+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ አመት 12ኛ መደበኛ ስብሰባ በኮሪደር ልማት ሥራዎች ላይ ተወያይቶ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እና ውሳኔ ተላልፏል።

በኮሪደር ልማት ሥራው ሂደት ያለበት ደረጃ እና በሂደት ለሥራው መሳለጥ የተወሰደው የተቀናጀ አመራር ሂደት ለካቢኔ አባላት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ፤ በውይይቱም ከፍተኛ አመራሩ በጥብቅ የሥራ ዲስፕሊን መመራቱን እና የተሰጠው አቅጣጫ ፤ድጋፍ፣ ክትትል ለከተማው ትልቅ ተሞክሮ ያሳየ መሆኑ ተገልጿል ።

የልማት ሥራው ከ35ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በግንባታ ግብአቶች ላይ ሰፊ የገበያ ትስስር የፈጠረ መሆኑ

. ከ48 ኪ.ሜ በላይ የተሽከርካሪ የመንገድ ልማት፣ 4 የመሬት ውስጥ የእግረኛ መንገዶች የያዘ መሆኑ

. 96 ኪ.ሜ ሰፋፊ የእግረኛና 100 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገዶች በከፍተኛ ጥራት እየተሰራ መሆኑ

. የ5ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ፣ 48 የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን የሚያሳልጡ የአውቶቡስ እና የታክሲ ተርሚናሎችንና መጫኛ ማውረጃ ስፍራዎች በግንባታ ሂደት ላይ መሆናቸው

በጥቅሉ ከ 240 ኪ.ሜ በላይ የሚሆን የመንገድ እና ተያያዥ መሰረተ ልማት ግንባታዎች በከፍተኛ ጥራት እየተከናወነ መሆኑ ኣቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል

. 70 የከተማን ውበት የሚጨምሩ የህዝብ መናፈሻ ስፍራዎች፣ ፋውንቴኖችና የአረንጏዴ ስፍራዎች፣ የመዝናኛና የመናፈሻ ስፍራዎች፣ የልጆች መጫዎቻና የህዝብ ፕላዛዎች፣ 120 የሚሆኑ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የከተማዋን ማዘጋጃዊ አገልግሎቶችን ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ የፍሳሽ ማስተላለፊያዎች፣ ከተማችንን የሚመጥኑ የደህንነት ካሜራዎች፣ የብልህ ትራንስፖርት ስርዓት ( intelligent transport system) በመሬት ውስጥ የመዘርጋት ስራዎች ፤

. ከ400 በላይ ህንጻዎች እንዲታደሱ የማድረግ እንዲሁም የከተማዋን ደረጃ የሚመጥኑ የቀለምና የመብራት ስራዎች እና ሌሎች በርካታ ግንባታዎችን በከፍተኛ ትጋት እና የሥራ ጥራት መሰራታቸው ለከተማዊ ትልቅ ተሞክሮ መሆኑን በጥንካሬ ተነስቷል

በግንባታ ላይ የሚገኙት ስራዎች ሲጠናቀቁ አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ ና አበባ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዲሁም እየጨመረ የመጣውን የመዲናችንን ዓለምአቀፍ የስበት ማዕከል ና ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ በማሳካት ረገድ የላቀ ሚና የሚጫወቱ መሆኑን ካቢኔው ተወያይቷል ። ይህንኑ የሥራ ጥንካሬ እና ልማት እውን እንዲሆን በቀጣይ ቀናት በርብርብ እና በተጀመረበት የጥንካሬ መንፈስ ስራውን ማጠናቀቅ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል::

ከተማዋን ነዋሪዎች ንፁህ ምቹ እና ደረጃውን ወደጠበቀ መኖሪያ ቤቶች የተደረገው ዝውውር በጥሩ ተሞክሮ የተነሳ ሲሆን አሁንም አልፈው የሚነሱ የህብረተሰብ ቅሬታዎች በትኩረት ማዳመጥ እና ምላሽ መስጠት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።የሀገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ብቃት እና ፍጥነት እንዲሁም 24 /7 የመስራት ባህል ያደገበት እና በግልተቋማት እና በመንግስት መተማመን ያሳደገ የሥራ ልምምድ መሆኑም በካቢኔ አባላቱ በጥንካሬ ተነስቷል ፡ ፡

ይህን ተሞክሮ ይዞ በቀጣይ የዝናቡ መጠን ሳይጨምር ሥራዎችን በጥራት እና በተጀመረበት ፍጥነት መጨረስ እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የኮሪደር ልማት ግዢን በተመለከተ የከተማውን ሀብት ባማከለ መልኩ በቁጠባ እና በጥራት ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር የተደረገው መናበብ እና ውይይት በጥንካሬ መቀጠል እንዳለበት እና ለሀገር ውስጥ ተቋራጮች የተፈጠረው እድል የከተማዋን ስራ ዕድል እና በአብዛኛው በራስ አቅም ለመገንባት የተሄደበት መሆኑ ተጠቅሷል::

አዲስ አበባ ላይ አቅዶ መጨረስ 24/7 መስራት ባህል ብቻ ሳይሆን መደበኛ የስራ ባህላችን ሁኗል::

Comments are closed.