መንገዶቻችን ለረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የዝናብ ውሃ መውረጃ መስመሮችን ከጉዳት እንጠብቅ!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የመንገድ ዳር ውሃ መፋሰሻ መስመሮች ደህንነት ለማረጋገጥ፤ በየጊዜው የድሬኔጅ መስመሮችን እየፈተሸ መጠነ ሰፊ ፅዳትና ጥገና ስራ እንደሚያከናውን ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ዛሬም ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በዝናብ ውሃ መውረጃ መስመሮች ውስጥ በተደጋጋሚ የሚጣለው ደረቅ ቆሻሻ የከተማዋን ፅዳትና ውበት ከማጓደሉም ባሻገር፣ በከፍተኛ ወጪ የተገነባውን የመንገድ መሠረተ-ልማት ለብልሽት እያጋለጠው ይገኛል፡፡
ይህን አሳሳቢ ጉዳይ አቅልለን ሳንመለከት፣ በየአካባቢያችን የሚታዩ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በባለቤትነት ስሜት ካልተከላከልን፤ የጋራ መጠቀሚያችን የሆነው የመንገድ ሃብት ለከፍተኛ ጉዳት ከመዳረጉም በላይ፣ ነዋሪዎችን በክረምት ወቅት ለሚከሰት የጎርፍ አደጋ ማጋለጡ አይቀሬ ነው፡፡
በሌላም በኩል ከተለያዩ ከተቋማትና ከመኖሪያ ቤቶች ወደ መንገድ የሚለቀቀው ፍሳሽ ቆሻሻም የእግረኛና የአስፋልት መንገድን ከማበላሸቱም በተጨማሪ ለህብረተሰቡ የጤና ጠንቅ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
በመሆኑም የዝናብ ውሃ መፍሰሻ መስመሮች ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ እንዲውሉ የበኩላችንን ኃላፊነት በመወጣትና ህገ-ወጥ ድርጊት ፈፃሚዎች እንዲታረሙ በማድረግ፤ አካባቢያችንን ከብክለትና የመንገድ ሃብታችንን ከጉዳት እንዲሁም ህብረተሰባችንን ከጎርፍ አደጋ ስጋትና ከጤና መታወክ በጋራ እንድንከላከል የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
የተሻለ መንገድ፣ ለተሻለች አዲስ አበባ!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ፡- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369