+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ የመረጃ አያያዝ ሶፍትዌር ስራ ላይ ለማዋል ስልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19 ቀን 2016ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ስርዓት/Integrated civil service management information system/ ስራ ላይ ለማዋል ለሚመለከታቸው የስራ ክፍል ቡድን መሪዎችና ባለሞያዎች የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የስልጠና ማዕከል ዳይሬክቶሬት ኃላፊ አቶ መስፍን ከበረ የስልጠናው ዋና ዓላማ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ስርዓትን ስራ ላይ በማዋል የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የሰው ሀብት የመረጃ አደረጃጀት በማዘመን የዕለት ተዕለት ተግባራትን ከማኑዋል ይልቅ በሲስተም ዳታ ቤዝ የታገዘ ዘመናዊ አሰራር የተከተለ እንዲሆን ለማስቻል ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናውን ለመስጠት ከፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከመጡ ባለሞያዎች መካከል አቶ አሸናፊ በላይ በበኩላቸው በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በመንግስት ተቋማት በስራ ላይ ያለውን የመረጃ አያያዝና የአሰራር ስርዓት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማስደገፍ የሰራተኞችን መረጃ በአንድ ቋት ለማስቀመጥ የሚረዳ ሶፍትዌር ነው ብለዋል፡፡

ሶፍትዌሩ በመንግስት ተቋማት እስከ አሁን እየተሰራበት የሚገኘውን የሲቪል ሠራተኛ ቅጥር፣ የደረጃ እድገት፣ ዝውውር፣ ስንብትና የመሳሰሉ የሰው ሀብት አስተዳደር አሰራሮችን ቀልጣፋ ለማድረግና መረጃዎችን በዘመናዊ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማደራጀት፣ ቀላል እና ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን አቶ አቶ አሸናፊ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.