በ5ኛው የህብረት ስምምነት ሰነድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18 ቀን 2016ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ጋር በመተባበር ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ ሰራተኞች 5ኛው የህብረት ስምምነት ሰነድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሶስት ዙር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ተሰጠ ፡፡
ሥልጠናው ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋም ለውጥና ድጋፍ ሰጪ ዘርፍ አማካሪ አቶ አብደላ ረዲ በ5ኛው የህብረት ስምምነት ሰነድ ላይ የአሰሪውና ሰራተኛው መብትና ግዴታ በተመለከተ ለሰራተኛው በቂ ግንዛቤ በመፍጠር በተቋሙና በሰራተኛው መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ አብደላ አያይዘውም የስልጠናው ተሳታፊዎች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት ለሌሎች ሰራተኞች በማጋራትና የህብረት ስምምነት ሰነዱ ላይ ያልተካተቱ በቀጣይ ቢካተቱ ብለው የሚያስቧቸውን ሀሳቦች ዙሪያ ግብዓት በመስጠት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የባለስልጣኑ የሰው ኃብትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬተር ዳይሬክተር አቶ ተሾመ አሰፋ በበኩላቸው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የህብረት ስምምነቱን በአግባቡ ተረድተው ተግባር ላይ ከማዋል አንፃር የሚታየውን የግንዛቤ ክፍተት በመሙላት ረገድ ስልጠናው መሰጠቱ የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው 5ኛው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህብረት ስምምነቱ ያካተታቸው የአሰሪ እና ሰራተኛ መብት ፣ ግዴታና መሰል ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ እንደረዳቸው ገልፀዋል፡፡
ለ5ኛ ጊዜ ተሻሻሎ የፀደቀው የህብረት ስምምነት ከጥቅምት 2015 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ ማዋሉ ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity