+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም የውጭ ቀለበት መንገድ ግንባታ በቅርቡ አስፋልት የማልበስ ሥራ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን እያስገነባው የሚገኘው የቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም የውጭ ቀለበት መንገድ ፕሮጀክት በተሻለ የግንባታ አፈፃፀም ላይ ይገኛል፡፡ይህ የመንገድ ፕሮጀክት አጠቃላይ 1.4 ኪ.ሜትር ርዝመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ 20 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡ የግንባታ ስራውን ዲሪባ ደፈረሻ የተባለ የስራ ተቋራጭ ከ185.5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ዋጋ እያከናወነው ሲሆን የማማከርና የግንባታ ቁጥጥሩን ጎንድዋና አማካሪ ድርጀት እየተከታተለው ይገኛል፡፡ አሁን ላይ በመንገድ ፕሮጀክቱ የግራ መስመር ላይ 800 ሜትር የሚሆነው የሰብ ቤዝና የከርቭ ስቶን ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡ በቅርቡም አስፋልት የማልበስ ሥራ ይጀመራል።ከዚህ በተጨማሪም በሁለቱም አቅጣጫ የገረጋንቲ አፈር ሙሌት፣ የከልቨርት ቦክስ፣ የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ እና የማንሆል ስራዎች በመገባደድ ላይ ይገኛሉ፡፡ይሁን እንጂ በፕሮጀክቱ የቀኝ መስመር 300 ሚሊ ሜትር ውፍረት ያለው የውሀ መስመር ባለመነሳቱ ግንባታው ላይ የተወሰነ መጓተት ፈጥሯል፡፡ የውሃ መስመሩን አጭር ጊዜ ውስጥ ከመንገድ ግንባታ የወሰን ክልል ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ለማስነሳት ቀሪ የመንገድ ግንባታ ስራውን ለመቀጠል የስራ ተቋራጩ ተጨማሪ ኮንትራት ወስዶ እየሰራ ይገኛል፡፡ባለስልጣኑ እስከ ተያዘው በጀት ዓመት ማብቂያ ድረስ የመንገዱን የግራ መስመር ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እና በቀኝ በኩል ያለውን ደግሞ የወሰን ማስከበሩን ስራ አጠናቆ የሰብ ቤዝ ደረጃ ላይ ለማድረስ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡

2 Responses to “የቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም የውጭ ቀለበት መንገድ ግንባታ በቅርቡ አስፋልት የማልበስ ሥራ ይጀመራል

  • cheap priligy 25 to prevent rebound

  • The 1 month postoperative Vario topographic analysis showed how CONTOURA Vision treatment left a smooth, beautiful topographic contour to the cornea with virtually no topographic abnormalities remaining buy priligy pills Yes, we went over the Vitamin K problem a few topics ago

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *