+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ አደባባይን በማንሳት በትራፊክ መብራት የመቀየር ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በተለምዶ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን አደባባይ በማንሳት በትራፊክ መብራት የመቀየር ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

በአካባቢው እየጨመረ በመጣው ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ሳቢያ በአደባባዩ ላይ አሽከርካሪዎች ረጅም ጊዜ በመጠበቅ ለማለፍ ይገደዱ እንደነበር ይታወሳል።

በአካባቢው እየተፈጠረ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ለመፍታት አደባባዩን ሙሉ በሙሉ በማንሳት ወደ ትራፊክ መብራት የመቀየር ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ የአፈር ቆረጣ፣ የድጋፍ ግንብ እና የሙሌት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ የከርቭ ስቶን፣ የአስፋልት ማልበስ እና የትራፊክ መብራት የተከላ ስራዎችን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ ቀንና ሌሊት እየተሰራ ይገኛል፡፡

የቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ አደባባይ ማሻሻያ ስራ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፣ ከጦር ኃይሎች ወደ አየር ጤና የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በአውጉስታ በኩል ወደ ዘነበ ወርቅ – አየር ጤና እንዲሁም ከአየር ጤና በቶታል ወደ ብስራተ ገብርኤል አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ደግሞ በአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን – ቆሬ አደባባይ የሚወስደውን መንገድ እንዲጠቀሙ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያሳስባል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.