+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የፈረንሳይ ኤምባሲ- አቦ ቤተክርስቲያን የመንገድ ግንባታ አሁናዊ ገፅታ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26 ቀን 2016 ዓ.ም፡-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በራስ ኃይል ከሚገነባቸው መንገዶች መካከል አንዱ የሆነውን የፈረንሳይ ኤምባሲ- አቦ ቤተክርስቲያን የመንገድ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 1.2 ኪ.ሜ ርዘመትና 15 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥም አንድ ኪሎ ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል በመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ተሸፍኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የእግረኛ መንገድ፣ የመንገድ ዳር መብራት፣ የድልድይና የድጋፍ ግንብ ስራዎችም ጎን ለጎን ተከናውነው የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል፡፡

በቀሪው 200 ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል ደግሞ የከርቭ ስቶን፣ የሰብ ቤዝና የቤዝ ኮርስ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥም የአስፋልት ስራውን ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ አሁን ላይ የፕሮጄክቱ አጠቃላይ አፈፃፀም ከ90 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሲሆን ከ6 ኪሎ እና አካባቢው ተነስተው ወደ ፈረንሳይ ፓርክ፣ ፈረንሳይ አቦ ቤተክርስቲያን እና አካባቢው ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች አማራጭና አቋራጭ መንገድ በመሆን የሚያገለግል ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.