እግረኞችን ታሳቢ ያደረገው የከተማዋ የመንገድ መሠረተ-ልማት
የእግር ጉዞ አጫጭር እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ሂደት የትራንስፖርት ወጪን የሚቀነስ፣ የተለያዩ የትራንስፖርት መጓጓዣዎችን መጠቀም ሳያስፈልግ፣ በፈለጉት ጊዜ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በቀላሉ ለመዘዋወር የሚያስችል ተመራጭ አማራጭ ከመሆኑም ባሻገር ጤንነትን ለመጠበቅ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ይታመናል፡፡
የከተማችን ነዋሪዎች በእግር ለሚያካሂዱት እንቅስቃሴ ደግሞ፤ የሚኖሩበትን ከተማ ዕድገት የሚመጥን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ምቹና ዘመናዊ የእግረኛ መንገዶች በሁሉም ሥፍራዎች መገንባት ያስፈልጋል፡፡
ይህንን እሳቤ መሠረት በማድረግ አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት 5 ዓመታት ካከናወናቸው ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች ጎን ለጎን ዘመናዊ እና ሁሉን አቀፍ ዲዛይን የተካተተባቸው የእግረኛ መንገዶችን በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ሲገነባ ቆይቷል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለይም ከ2009 በጀት ዓመት ጀምሮ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የገነባቸው የእግረኛ መንገዶች በአጠቃቀም ጉድለት ለጉዳት እየተጋለጡ መሆኑ የአደባባይ እውነታ ቢሆንም፣ ከዲዛይን ዝግጅታቸው ጨምሮ እስከ ግንባታ ትገበራቸው ድረስ ያለው ይዘት ለእግረኞች እንቅስቃሴ ምቾት የሚሰጡ ናቸው፡፡
በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጋር ተቀናጅቶ እየተዋበ የሚገኘው የመንገድ አካፋይና ዳርቻዎች የዕፅዋት ሽፋን እግረኞች በምቾት እንዲንቀሳቀሱ፣ ድካም ሲሰማቸውም የሚያርፉባቸው እና መንፈሳቸውን የሚያድሱባቸው በህብረ-ቀለማት በደመቁ አበቦች የታጀቡ መቀመጫ ወንበሮች ጭምር የተካተቱባቸው ሆነዋል፡፡
ለዕይታ ማራኪና ለከተማዋ ድምቀት፣ ለእግር ጉዞ ደግሞ ምቹ ሆነው የተገነቡትን የእግረኛ መንገዶችና የመንገድ ዳር እፅዋቶችን የመንከባከብና በአግባቡ የመጠቀም የጋራ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ መልዕክታችን ይድረሳችሁ፡፡
መልካም ቀን!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity