+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር የባለስልጣኑ ሠራተኞች የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች በድምቀት የሚከበረውን የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የበኩላቸውን አወንታዊ ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የጥምቀት በዓል አከባበርን አስመልክቶ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታከለ ሉለና የአብሮነት መገለጫ የሆነውን የጥምቀት በዓል ቱፊቱን ጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ በበኩላቸው የጥምቀት በዓል ቱሪስቶች በስፋት የሚታደሙበት ስለሆነ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

በዓሉ በሚከበርባቸው ሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ላይ የመንገድ ዳር መብራቶች እና ሌሎች የመንገድ መሰረተ ልማቶች ለታደሚዎች ምቹ መሆናቸውን በማረጋገጥ በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲያልፍ ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግብረ ሀይል አቋቁሞ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.