የቀጨኔ ቁስቋም አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1 ቀን 2016፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በራሱ አቅም በከተማዋ እየገነባቸው ካሉ በርካታ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የቀጨኔ ቁስቋም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ ሃይል እየገነባው የሚገኘው የቀጨኔ ቁስቋም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት አጠቃላይ 1.4 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 16 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡
በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ የአስፋልት ስራው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪውን የቀለም ቅብ እና የፅዳት ስራ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
መንገዱ በዋናነት ከቀጨኔ መስመር ተነስቶ ሽሮ ሜዳ ቁስቋም የሚያገናኝ ሲሆን በአካባቢው ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ከመቅረፍ ባሻገር የዕለት ተዕለት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ከማሳደግ አኳያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity