+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለተገልጋዮች ምቹ ለማድረግ የመቃረቢያና የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታና ጥገና ተከናወነ

መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን፤ በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች እያካሄደ ከሚገኘው መጠነ ሰፊ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ ጎን ለጎን፤ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በከተማዋ በሚገኙ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የመቃረቢያና የውስጥ ለውስጥ መንገድ መልሶ ግንባታና ጥገና አካሂዷል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት ዓመታትም ለትምህርት እና ለህክምና መስጫ ተቋማት ተመሳሳይ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን፣ በያዝነው በጀት ዓመትም በልደታ ክፍለ ከተማ ለተስፋ ብርሃን የህፃናት ማቆያና ምገባ ማዕከል የመቃረቢያ የአስፋልት መንገድ ሰርቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም፤ በአራዳ ክፍለ ከተማ ለአፍሪካ አንድነት ቁጥር 2 የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመልሶ ግንባታና ጥገና ደረጃ የአስፋልት መቃረቢያ መንገድና የምድረ ግቢ አስፋልት ሥራ በማከናወን ለትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደት ስምረት የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.