+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚያግዝ፣ በአደጋ ተጋላጭነትና በመንገድ ደህንነት ላይ ያተኮረ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

መስከረም 9 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በማሽከርከር ሙያ ላይ ለተሰማሩ የባለሥልጣኑ ሰራተኞች በአደጋ ተጋላጭነትና በመንገድ ደህንነት ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

ሥልጠናው በተቋሙ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታና ጥገና ስራዎች ላይ በቀላልና ከባድ መኪና አሽከርካሪነት የሙያ መስክ የተሰማሩ ሰራተኞች አቅማቸውን እንዲያሳድጉ እና ከትራፊክ አደጋ በፀዳ ሁኔታ የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያግዝ ነው፡፡

በአራት ዙር ተከፍሎ በመስጠት ላይ የሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና በአደጋ ተጋላጭነትና በመንገድ ደህንነት ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ስልጠናው ብቁና በሥነ-ምግባር የታነፀ አሽከርካሪን በማበራከትና የትራፊክ ደህንነትን በማረጋገጥ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት በኢትዮጵያ መድህን ድርጅት የካሳ ክፍል ኃላፊ አቶ መልካሙ ሙሉነህ እንደገለፁት ስልጠናው በትራፊክ አደጋ መንስኤዎች፤ በቅድመ ጥንቃቄ ተግባራት እና በሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ላይ ሰልጣኞች የተሻለ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ያግዛል ብለዋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሰው ኃብት ልማት እና ስራ አፈፃፀም ማኔጅመንት ቡድን ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ ስልጠና ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፣ በስልጠናው ላይ 250 የሚሆኑ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እንደሚያሳትፉ ይጠበቃል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.