“በአገልጋይነት ቀን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች የታየው አርአያነት ያለው አገልግሎት አሠጣጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ አሳሰቡ
አዲስ አበባ፡ ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ ያሳዩት ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ በ2016 በጀት ዓመትም ባህል ሆኖ መቀጠል እንዳለበት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ አሳስበዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በሠንደቅ ዓላማ የማውረድ ሥነ-ስርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በአገልጋይነት ቀን የባለስልጣኑ ሠራተኞች ተገልጋዮችን በቅንነት በማገልገል ረገድ ያሳዩት ቁርጠኝነት የሚበረታታና ተቋሙን ለላቀ ስኬት የሚያዘጋጅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኢንጂነር ሞገስ አክለውም ባለስልጣኑ በ2016 በጀት ዓመት በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታና ጥገና የህብረተሰቡን ፍለጎት ከማሳካት አንፃር በሚያደርገው ርብርብ የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች የአገልጋይነት ባህላቸውን በማሳደግ ከፍተኛውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
