+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የመስዋዕትነት ቀን በተለያዩ መርሀ-ግብሮች በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተከብሮ ውሏል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2 ቀን 2015፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ጳጉሜ 2 የመሰዋዕትነት ቀንን አስመልክቶ “በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች አክብረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የተቋም ለውጥና ድጋፍ ሰጪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ደፋር በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የመሰዋዕትነት ቀን ሲታሰብ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገራችንን ዳር ደንበር ለማስከበር የከፈለውን መስዕዋትነት በማሰብ ያለንን አክብሮት የምንገልፅበት ቀን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ ዘመናት ኢትዮጵያ ሀገራችን የገጠሟትን ፈተናዎች በመሻገር ረገድ ኢትዮጵያን በጋራ በመተባበር ህይወታቸውን ጭምር በመሰዋት ሀገራችንን አቆይተውልናል፤ አሁንም በህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት መንፈስ አንድነታችንን አጠናክረን ማስቀጠል እንደሚገባን አቶ ታደሰ አክለው ገልፀዋል፡፡

አቶ ታደስ አያይዘውም በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ታላቅ ተጋድሎ የቆመችን ሀገርን ወደፊት ለማሻገር ሁሉም በተሰማራበት መስክ መስዋዕትነት መክፈል ይገባዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.