+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአዲስ አመት ዋዜማ ክዋኔዎች

አዲስ አበባ፣ጳጉሜ 1 ቀን 2015 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የአዲስ አመት ዋዜማን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ በርካታ ስራዎችን የከተማዋን ጎዳናዎች የማደስ፣ የማጽዳትና የማስዋብ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ለማኅበረሰቡ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛነት ያላቸው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ጳጉሜን 1 የአገልጋይነት ቀን “ኢትዮጵያን እናገልግል” በሚል መሪ ሃሳብ በአገልጋይነት መንፈስ በርካታ ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች መጪው አዲስ አመትን በብሩህ ተስፋ ለመቀበል ከተማዋን ንጹህና ጽዱ ለማድረግ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የከተማዋን ጎዳናዎች የማደስ፣ የማጽዳትና የማስዋብ ስራዎችን እየሰሩ ነው፡፡

የጥገና፣ የማስዋብና ጽዳት ስራዎች ከተከናወኑባቸው አካባቢዎች መካከል ከሩዋንዳ – አትላስ፣ ኡራኤል አደባባይ፣ ከቴዎድሮስ አደባባይ – ተክለኃይማኖት፣ ከቄራ – ጎተራ ማሳለጫ፣ ከአፍንጮ በር – ጊዮርጊስ ቀይመስቀል፣ ደጃች ውቤ፣ ከቤተዛታ ሆስፒታል – ጊዮን ሆቴል፣ ከኤልያና ሞል – ቴዎድሮስ አደባባይ፣ ከለገሀር – ፒያሳ፣ ከደንበል – ባንቢስ እንዲሁም ዮርዳኖስ ሆቴለ አካባቢ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.