+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ለመጪው አዲስ ዓመት – ጎዳናም እንደ ቤት እየተዋበ ነው

አዲስ ዓመት፤ ብሩህ ተስፋ ሰንቀን፣ ነገን በተሻለ ዕይታ የምንቀበልበት የዘመን ሽግግር ምዕራፍ እንደሆነ ይታወቃል።

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ፤ የትናንት ጉድለቶቻችን ተስተካክለውና ተሟልተው፣ የተሻለ ነገ እንዲኖረን ከመመኘት ባለፈ ዕቅዶቻችንን ገቢራዊ ለማድረግ የምንደረደርበት ልዩ ወቅት ነው – የአዲስ ዓመት መባቻ።

በመሆኑም በአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ አቅም በፈቀደ መጠን፣ በዓሉን ለማድመቅ፣ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ፣ ቤትና ቀዬን ማስዋብ፣ ማፅዳትና ለዕይታ ማራኪ ማድረግ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጩ ዓለም የተለመደ ተግባር ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣንም መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ በመደበኛነት ከሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራዎች በተጨማሪ፣ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች በዘመቻ መልክ የመንገድ አካላት ጥገና እና ጽዳት፡ እንዲሁም የማስዋብ ስራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል፡፡

እንደሚታወቀው እያገባደድነው ያለው የ2015 የበልግ ወቅት ዝናብ በመራዘሙና ከዋናው የክረምት የዝናብ ወቅት ጋር የገጠመ በመሆኑ በተከታታይ ከ6 ወራት ያላነሰ የዝናብ ወቅት አሳልፈናል።

ይህም በአጠቃቀም ጉድለት በተደጋጋሚ በድሬኔጅ መስመሮች ላይ ይደርስ ከነበረው ጉዳት ጋር ተዳምሮ አንዳንድ የከተማዋ መንገዶች ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ እንዲሆኑ አድርጓል።

ይህንን ችግር ለመፍታት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያየ ምክንያት ብልሽት የገጠማቸውን እና የተቦረቦሩ የአስፋልት መንገዶችን፣ በቆሻሻ የተደፈኑ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን ከመጠገንና ከማስተካከል ጎን ለጎን፣ በእግረኛ መንገድ ላይ የተከማቹ ቆሻሻዎች፣ የግንባታ ግብዓትና ተረፈ ምርቶችን በማንሳት፣ አደባባዮች እና የመንገድ አካፋዮችን ቀለም በመቀባትና የመንገድ ዳር መብራቶችን በመጠገን የከተማዋን ጎዳናዎች እያስዋበ ይገኛል፡፡

ሰናይ ዘመን ይሁንልዎ!

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.