በእግረኛና ተሸከርካሪ መተላለፊያ መስመር ላይ የግንባታ ግብዓትና ተረፈ-ምርት በሚያከማቹ አካላት ላይ የሚወሰደው የእርምት እርምጃ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተሸከርካሪ እና የእግረኛ መንገዶች ላይ የግንባታ ግብአትና ተረፈ ምርት ባስቀመጡ አካላት ላይ የጀመረውን የእርምት እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በንፋ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ከአደይ አበባ ወደ አዲስ ሰፈር በሚወስደው መንገድ ላይ የግንባታ ግብዓት እና ተረፈ ምርት ያስቀመጡ ግለሰቦች ከህገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲታረሙ በተደጋጋሚ የቃልና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ባለመቻላቸው የደቡብ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር ከትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣ ከወረዳው ፖሊስ እና ደንብ ማስከበር ጋር በመቀናጀት በመንገድ ላይ የተከማቸው አሸዋና ጠጠር እንዲነሳ አድርጓል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ህገ-ወጥ ተግባር በከፍተኛ ወጪ የተገነቡትን የመንገድ ሀብቶች ለከፍተኛ ጉዳት እያጋለጠ ከመሆኑም ባሻገር የትራፊክ እንቅስቃሴውን በማስተጓጎል ህብረተሰቡን ለትራፊክ አደጋ እያጋለጠ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ባለሥልጣኑ በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች በመንገድ ላይ የግንባታ ግብአትና ተረፈ ምርት ያከማቹ፣ የተሸከርካሪ አካላት ጥገና ሥራ የሚያከናውኑ፣ የተሽከርካሪ እጥበትና በእግረኛ መንገድ ላይ መኪና የሚያቆሙ አካላት ከህገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ እያሳሰበ፤ ማሳሰቢያውን ተግባራዊ በማያደርጉት ላይ የማስተካከያ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ ይገልፃል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
