+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እንደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሁላችንንም ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው”

ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ

ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ቃል በከተማዋ ኮሙኒኬሽን መዋቅር ስር የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የሚዲያ ተቋማት አመራሮችና ታዋቂ ግለሰቦች የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ተከናውኗል።

ኘሮግራሙን በንግግር የከፈቱት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እንደህዳሴ ግድብ ግንባታ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን በመግለፅ፣ በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር መሳተፋችን፣ መላው የከተማዋ የኮሙኒኬሽን መዋቅር አባላትና የሚዲያ አመራሮች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስኬት በግንባር ቀደምትነት መሰለፋችንን ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል።

በቀጣይም ሰኞ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ. ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተዘጋጀው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ንቁ ተሳታፊ ከመሆን ባለፈ ህብረተሰባችን በንቃት እንዲሳተፍና የተተከሉ ችግኞችን እንዲንከባከብ በማነቃቀት በኩል የኮሙኒኬሽን መዋቅሩ፣ የሚዲያው እና የታዋቂ ሰዎች ሚና ከፍ ያለ በመሆኑ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በኘሮግራሙ ላይ በከተማዋ በኮሙዩኒኬሽን መዋቅር ስር የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም የመንግስትና የግል ሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.