በአራዳ ህንፃ አካባቢ የድሬነጅ መስመር መልሶ ግንባታ እና ፅዳት ተከናነወነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሰልጣን የከተማዋን የመንገድ ዳር ውሃ መፋሰሻ መስመሮች ደህንነት በመፈተሽ የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ሥራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
በተለይም በክረምት ወራት የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ ስጋት ታሳቢ በማድረግ በተለያዩ የከተማዋ ማዕዘናት የጎርፍ አደጋ ቅድመ መከላከል ሥራዎች እያከናወነ ነው፡፡ በዚህ ሣምንት የድሬነጅ መስመር መልሶ ግንባታ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል የአራዳ ህንፃ አካባቢ ተጠቃሽ ነው፡፡
ቀደም በአካባቢው የነበረውን የድሬነጅ መስመር ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ባለስልጣኑ 75 ሜትር ርዝመት ያለው የድሬነጅ መስመር የመልሶ ግንባታ እና የፅዳት ስራ ያከናወነ ሲሆን መንገዱን ለትራፊክ ፍሰት ምቹ ለማድረግም የአስፋልት ጥገና ስራ አከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity