+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች በመልሶ ግንባታ ደረጃ የአስፋልት ጥገና ስራ እየተከናወነ ነው

መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያየ ምክንያት ለብልሽት የተዳረጉ አቋራጭ የአስፋልት መንገዶችን በመለየት በመልሶ ግንባታ ደረጃ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዋና ዋና መንገዶች ላይ እያከናወነ ከሚገኘው የመንገድ ጥገና ስራ ጎን ለጎን፣ የትራፊክ ፍሰቱን በማቀላጠፍ አስተዋፅኦ ያላቸው አቋራጭ መንገዶችን እየጠገነ ይገኛል፡፡

በመልሶ ግንባታ ደረጃ የጥገና ስራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከፈረንሳይ ጉራራ – አንቆርጫ ድልድይ የሚወስደው መንገድ ይገኝበታል፡፡ በዚህ መንገድ ላይ የተከናወነው የጥገና ስራ 1.5 ኪ.ሜትር ርዝመት እና 9 ሜትር የጐን ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከጎፋ መብራት ኃይል ወደ ሳሪስ አደይ አበባ በሚወስደው አቋራጭ መንገድ ላይ 780 ሜትር ርዝመትና 10 ሜትር የጐን ስፋት የሚሸፍን የጥገና ስራ በመከናወን ላይ ነው፡፡

በመልሶ ግንባታ ደረጃ የሚከናወነው ጥገና ስራ የተጐዳውን አስፋልት ሙሉ በሙሉ በማንሳት የሚከናወን ሲሆን ስራው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በአካባቢው የሚኖረውን የትራፊክ ፍሰት ምቹ ከማድረጉም በተጨማሪ የትራፊክ መጨናነቁን የሚያቃልል ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.