ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አራዳ ህንፃ የሚወስደው መንገድ ተጠገነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13 ቀን ፣ 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በአገልግሎት ጫና፣በአጠቃቀም ችግርና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ለብልሽት የተዳረጉ መንገዶችን በመለየት የጥገና ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
በያዝነው ሳምንት የጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከቴዎድሮስ አደባባይ -ኤሊያ ሆቴል እንዲሁም ከአራዳ ህንፃ ወደ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት የሚወስደው መንገድ ተጠቃሽ ነው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኤሊያና ሆቴል የሚወስደው መንገድ 170 ሜትር ርዝመት በ13 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን እንዲሁም ከአራዳ ህንፃ ወደ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት የሚወስደው መንገድ 100 ሜትር ርዝመት በ15 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን የአስፋልት መንገድ ጥገና አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity