የድልድይ ጥገና ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
መስከረም 26 ቀን 2015ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ለረጅም ዓመታት አገልግሎት በመስጠት የመፍረስ አደጋ የገጠማቸውን ድልድዮች በመለየት የጥገና ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የጥገና ስራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ በተለምዶ ፅዮን ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ድልድይ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም በክረምት ወራት በሚከሰት ጎርፍ እና ወደ ወንዝ በሚደፋ ቆሻሻ ምክንያት የመፍረስ አደጋ የተጋረጠበት ድልድይ በመሆኑ ለአካባቢው ነዋሪዎች ስጋት ሆኖ ቆይቷል፡፡
አሁን ላይ በመልሶግንባታ ደረጃ የአካባቢውን ነዋሪዎች ስጋት በሚቀርፍ መልኩ እየተሠራ የሚገኘው ድልድይ 4.5 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ከቀድሞ በተሻለ ሁኔታ ለመኪናም ሆነ ለእግረኛ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ በጥራት እየተጠገነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስርያ ቤቱ በያዝነው በጀት ዓመት ከሚያከናውናቸው መጠነ ሰፊ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች መካከል በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት የሚገኙና የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባቸውን 29 ድልድዮች በመለየት ለመጠገን አቅዶ እየሠራ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity