ባለስልጣኑ በ2014 በጀት ዓመት 891.7 ኪሎ ሜትር የግንባታና የጥገና ስራዎችን አከናወነ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2014 በጀት ዓመት 857.1 ኪሎ ሜትር ልዩ ልዩ የግንባታና የጥገና ስራዎች ለመስራት አቅዶ 891.7 ኪ.ሜ በማከናወን የእቅዱን 104 በመቶ ለማሳካት ችሏል፡፡
በበጀት ዓመቱ ውስጥ ከተከናወኑት የግንባታ ስራዎች መካከል 25.11 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 43.16 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 20 ኪ.ሜ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ 101.89 ኪ.ሜ የኮብል ንጣፍ፣ 15.55 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ፣ 0.164 ኪ.ሜ የዲሬኔጅ መስመሮች እና 0.041 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ስራዎችን የሚያካትት ሲሆን በድምሩም 205.97 ኪ.ሜ ይሸፍናሉ፡፡
በተመሳሳይ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 90.99 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 38.9 ከ.ሜ የጠጠር፣ 32.6 ኪ.ሜ የኮብል፣ 311 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳት፣ 8.39 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ዕድሳትና ጥገና፣ 0.05 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ የጥገና ስራ፣11.79 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ስራ እንዲሁም 192 ኪ.ሜ የመንገድ ቀለም ስራ በማከናወን በጠቅላላው 685.72 ኪ.ሜ የሚሆን ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራዎችን በበጀት ዓመቱ ውስጥ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity