+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ውድ የገጻችን ቤተሰቦች የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዴት እንቀንስ?

በተለይም ደግሞ የአስፋልት መንገዶችን ተከትለው የሚገነቡ የድሬኔጅ መስመሮችና ድልድልዮች ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል፡፡የፍሳሽ መስመሮች በቆሻሻ መደፈን መንገዶቻችንን በክረምት ወራት ይቅርና በበጋም ጭምር ውሃ የሚያመነጩ አድርጓቸዋል፡፡ በቅርቡ ሰሚት 72 አካባቢ የተፈጠረውን የመንገድ በውሃ መጥለቅለቅ ችግር ለማሳያነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ መንስኤው ደግሞ ህገወጥነት ነው፡፡ከታች ያሉት ምስሎቸ ለዚህ ምሰክር ናቸው፡፡ባለስልጣኑ የሚገነባቸው መንገዶች በቂ የውሃ መፋሰሻ መስመር እንዲኖራቸው በማድረግ የገነባና እየገነባ የሚገኝ ሲሆን፣ የድሬኔጅ መስመሮችን ደህንነት ለማረጋገጥ በየጊዜው የፅዳትና የጥገና ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ባሻገር ህብረተሰቡ የመንገድ ሀብቶችን በጋራ እንዲጠብቅና እንዲንከባከብ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ስራዎችን ከመስራት ባሻገርም በመንገድ ሃብትላይ ጉዳት የሚያደርሱ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ እያደረገ ይገኛል፡፡ይህም ሆኖ ዛሬም የመንገድ ሃብታችንን ለተጨማሪ ጉዳት እየዳረጉ የሚገኙ የተለያዩ ድርጊቶች በቸልተኝነት ሲፈፀሙ በስፋት ይስተዋላል፡፡ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት ያስችል ዘንድ በባለስልጣን መስሪያቤቱ በኩል እየተደረገ ካለው ጥረት ባሻገር ከባለድርሻ አካላት እና የመንገድ ሃብቱ ተጠቃሚና ዋነኛ ባለቤት ከሆነው የከተማችን ነዋሪ ምን ይጠበቃል ትላላችሁ?ለከተማችን የመንገድ ሃብት ደህንነት መረጋገጥ እና በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል ያግዛል የምትሉትን ገንቢ ሃሳብ እንድታጋሩ እንጋብዛለን፡፡በባለቤትነት ስሜት ለምትሰጡን ገንቢ አስተያየት በቅድሚያ እናመሰግናለን፡፡የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

Comments are closed.