+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ለባለስልጣኑ ሠራተኞች ሙያዊ ስነ-ምግባር ግንባታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

ሚያዝያ 29 ቀን 2017ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፦ ለአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሠራተኞች ብልሹ አሰራር መከላከልን ታላሚ ያደረገ የሙያ ስነ-ምግባር ግንባታ ስልጠና ተሰጠ ፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አባተ ገብረአምላክ እንደገለጹት በክህሎት፣ በእውቀትና በስነ-ምግባር የበቃ ባለሙያ መኖር የአንድን ተቋም ተልዕኮ በብቃት ለማሳካት ትልቅ ሚና ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ብቁና ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሰ የሰው ሃይል በመፍጠር በአገልግሎት አሰጣጡ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ያለመ እንደሆነ ገልጽዋል፡፡

ከስልጠናው ተካፋዮች አንዱ ኢንጂነር አለማየሁ አድማሱ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሙያዊ አቅምን ለመገንባት ከሚሰጡ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች ጎን ለጎን እንደዚህ አይነት ሙያዊ ስነ-ምግባር ላይ ትኩረት ያደረጉ የግንዘቤ ማስጨበጫ መድረኮች መኖራቸው ጠቀሜታው ከፍ ያለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ኢንጂነር አለማየሁ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስራ ባህሪይ ከተለያዩ ተቋማት እንዲሁም ከሕብረተሰቡ ጋር በቅርበት የሚሰራ እንደመሆኑ ሠራተኞች በተሰማሩበት ዘርፍ በሙያዊ ስነ-ምግባር የታገዘ ፈጣንና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት እንዲሰጡ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

በአራት ዙር ተከፍሎ በተካሄደው የብልሹ አሠራር መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ 420 የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ተካፋይ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር (X) ፡- https://twitter.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.