ከአየር ጤና – በአንፎ አደባባይ ወደ አምቦ መንገድ መጋጠሚያ የሚወስደው ጎዳና እየተጠገነ ነው
መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአየር ጤና – ኪዳነምህረት – በአንፎ አደበባይ አድርጎ ወደ አምቦ መጋጠሚያ መንገድ የሚወስደውን የአስፋልት ጎዳና እየጠገነ ይገኛል፡፡
በዚህ መስመር የሚከናወነው የመንገድ ጥገና በአጠቃላይ 2 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን ሲሆን፤ ከአየር ጤና – ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን እስከ ዓለም ባንክ ያለው የመንገዱ ክፍል የጥገና ስራ ተጠናቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡፡
አሁን ላይ ከዓለም ባንክ – አንፎ – አምቦ መንገድ መጋጠሚያ የሚወስደው ቀሪው መንገድ ክፍል በመጠገን ላይ ይገኛል፡፡
ይህ መስመር በምዕራብ አቅጣጫ ሌላው የከተማዋ ወጪ ገቢ ኮሪደር በመሆኑ የመንገዱ መጠገን በአካባቢው ያለውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማሳለጥ በኩል ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።
