+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የዓለም አቀፉ የፀረ- ፆታዊ ጥቃት ቀን ተከበረ

ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሠራተኞች የዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ፣ በአገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበውን የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን “የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል በድምቀት አክብረዋል፡፡

በራስ ኃይል መንገድ ግንባታ ሎት 4 በተካሄደው መርሃ-ግብር ላይ የሴቶችና ወጣቶች ቡድን መሪ ወ/ት ፀደንያ አበበ ባስተላለፋት መልዕክት፤ በየትኛውም ቦታና ሁኔታ በሴቶችም ሆነ በህፃናት ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ዜጎችን ለስነ-ልቦናዊና አካላዊ ጉዳት የሚዳርግና ለሞት የሚዳርግ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ ሊከላከለው እንደማገባ አሳስበዋል።

በውይይቱ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስርዓተ ፆታ ባለሙያ ወ/ት ማርታ ሰይድ ፆታዊ ጥቃትን በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ በጋራ ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ጠቁመው፤ ማህበረሰቡ ሰብአዊና ህገመንግስታዊ መብትና ግዴታዎችን አውቆ ለህጎች ተፈፃሚነት በጋራ እንዲሰራ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የውይይቱ ተሣታፊ የሆኑት ወ/ት ገነት ሙሉነህ 8ኩላቸው፤ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ጥቃት ትውልድን የሚጎዳ በመሆኑ ሁሉም ኃላፊነት ወስዶ መስራት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

Comments are closed.