+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሠጠት ላይ ነው

አዲስ አበባ፤ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በራስ አቅምና ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለተቋሙ ሰራተኞች አቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ከነሐሴ13 ቀን 2016 ጀምሮ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ትኩረት አድርጎ በመሰጠት ላይ በሚገኘው ሥልጠና የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የምህድስና ባለሙያዎች እየተካፈሉ ይገኛሉ፡፡

በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የሰው ሀብት ስልጠና ቡድን መሪ ወ/ሮ አስቴር ለገሰ፤ በ2017 በጀት ዓመት 4 ሺህ ለሚሆኑ የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ሰራተኞች በተመረጡ 45 ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት መታቀዱን ጠቅሰው፤ ከነሐሴ 13 ጀምሮ በ10 የስልጠና ርዕሶች ለ350 የተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ወ/ሮ አስቴር አያይዘውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት ከኮንስትራክሽን ማኔጅመት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በሌሎች አስር ርዕሰ ጉዳዮች ሙያዊ ስልጠና ይሰጣል ብለዋል፡፡

በኮንትራት እቅድና ግዥ አስተዳደር ላይ ስልጠና እየሰጡ የሚገኙት ኢንጅነር ዩሴፍ ኪዳኔ በበኩላቸው፤ በኮንስትራክሽን ስራዎች ውል አስተዳደርና የህግ አግባቦች እንዲሁም በሚያጋጥሙ ችግሮች አፈታትና መሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው፤ ስልጠናው በመስኩ የተሻለ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.

Comments are closed.