+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከ 2 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው 6 የትራፊክ ማሳለጫ ድልድዮች ተገንብተው ለትራፊክ ክፍት ተደርገዋል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ከ 2 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው 6 የትራፊክ ማሳለጫ ድልድዮች በመገንባት ለትራፊክ ክፍት ተደርጓል፡፡

ከዚህ በፊት ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ይስተዋልባቸው በነበሩ የቀለበት መንገድ ዋና ዋና መጋጠሚያ ሥፍራዎች እና በቃሊቲ -ቱሉ ዲምቱ መንገድ ላይ የተገነቡት እነዚህ የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድዮች አገልግሎት መስጠት በመጀመራቸው የትራፊክ ፍሰቱ በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻል አሳይቷል፡

የማሳለጫ ድልድዮቹ ከ50 ሜትር እስከ 600 ሜትር የሚደርስ ርዝመት እና ከ20 እስከ 50 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋትም አላቸው፡፡

እነዚህ የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድዮች በቃሊቲ – ቱሉ ድምቱ የመንገድ ፕሮጀክት ላይ ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ እና በተለምዶ ጋሪ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ የተገነቡትን ጨምሮ በኤምፔሪያል፣ በቦሌ ሚካኤል እና ለቡ የተገነቡት ያካትታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.