የስራ ላይ ደህንነት አጠባበቅ የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከቤት እሰከ ከተማ ማዕከል ጋር በመተባበር በመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎች ላይ ለተሰማሩ የተቋሙ ሠራተኞች በአደጋ መከላከል ላይ ያተኮረ የሙያ ደህንነትና የመሳሪያዎች አጠቃቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
በባለስልጣን መስሪያቤቱ የስልጠና ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መስፍን ከበረ እንደገለጹት ስልጠናው በመስክ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሰራተኞች መዘጋጀቱን ጠቁመው፣ ስልጠናው በሥራ ቦታ የሙያ ደህንነት አጠባበቅ እና የቅድመ መከላከል ዘዴዎች ላይ ሰልጣኞች ግንዛቤያቸውን እንዲያሳድጉ ያግዛል ብለዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት ከቤት እስከ ከተማ ማዕከል የሴፍቲ ባለሙያ አቶ ግዛው አበራ በበኩላቸው፣ የሥራ ላይ ደህንነትን ማረጋገጥ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ከሚገቡ አበይት ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችና ተቋማት የሥራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አሟልቶ ከማቅረብ ባለፈ፣ ቁሳቁሶቹ በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሠራተኞችን ግንዛቤ የሚያሳድጉ ሥልጠናዎች በየጊዜው መስጠት እና የሚታዩ ክፍተቶችን መሙላት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
የሥልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በተለያዩ ተቋማት ባጋጠሙ ተሞክሮዎች ላይ ተመስርቶ የተሰጠው የግንዛቤ ማዳበሪያ ሥልጠና በሥራ ላይ ደህንነትን አጠባበቅ ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል፡፡
በሥራ ላይ ደህንነት አጠባበቅ ትኩረት አድርጎ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተሰጠው ሥልጠና፤ በአደጋ መንስኤዎችና መከላከያዎች እንዲሁም በሥራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና በመሳሪያዎች አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የተሻለ መንገድ፣ ለተሻለች አዲስ አበባ!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ:-
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
