አስተዳደሩ በጃፓን ድጋፍ የተገዙ 79 ማሽኖችን ተረከበ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጃፓን መንግስት በሰጠው ድጋፍ የተገዙ 79 ለመንገድ ጥገና የሚያገለግሉ ማሽኖችንና ከባድ ተሽከርካሪዎች መረከቡን አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ “ለከተማችን ሁሉን አቀፍ ልማት የላቀ ፋይዳ ያላቸውን ዘመናዊ ሰፋፊ መንገዶችን እየገነባንና እያሰፋን ባለንበት ወቅት የተደረገልን ድጋፍ ትልቅ ፋይዳ አለው” ብለዋል::
የጃፓን መንግስት እና ሕዝብ እንዲሁም የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ላደረጉልን ድጋፍ በከተማ አስተዳደራችን ስም እናመሰግናለን ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
