+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከ8 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የኑሮ ድጎማ ድጋፍ ተደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን መጪዎቹን የፋሲካ እና የኢድ አል-ፈጥር በዓላት ምክንያት በማድረግ ከስድስት ሺህ ብር በታች የወር ደመወዝ ለሚያገኙ 4,367 ሠራተኞች 8 ሚሊዮን 734 ሺህ ብር ግምት ያላቸው የምግብ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የበዓል ድጋፉ ተጠቃሚ ለሆኑ የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ሠራተኞች ለእያንዳንዳቸው 2 ሺህ ብር ግምት ያላቸው 15 ኪሎ ግራም የስንዴ ዱቄትና 5 ሊትር የምግብ ዘይት ድጋፍ ተሰጥቷል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የተቋም ለውጥና ድጋፍ ሠጪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ደፋር እንደገለፁት፣ የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል በማዕድ ማጋራት፣ በኑሮ ድጎማ እና በሌሎች መስኮች እያካሄደው የሚገኘው ድጋፍ ማህበራዊ ችግሮችን በማቃለል በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጠቁመው፣ አሁን ላይ ለባለሥልጣ መስሪያቤቱ ሠራተኞች በተደረገው የኑሮ ድጎማ ድጋፍ ከተቋሙ አጠቃላይ ሠራተኞች ውስጥ 68 በመቶ የሚሆኑት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይም በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ከአራት ሺህ ብር በታች የወር ደመወዝ ለሚያገኙ 3,200 የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ሠራተኞች 10 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የጤፍ፣ የስንዴ ዱቄትና የዘይት ድጋፍ መደረጉ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.