+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በግንባታ ላይ የነበረው የካርል አደባባይ ለትራፊክ ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በካርል አደባባይ አካባቢ የሚታየውን የትራፊክ ፍስት የተቀላጠፈ ለማድረግ አደባባዩን የማንሳትና በትራፊክ መብራት የመተካት ሥራ ለማከናወን ካለፈው ቅዳሜ ምሽት ጀምሮ የመንገድ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል።

አሁን ላይ የአደባባይ ማንሳትና አስፋልት የማልበስ ሥራ ተገባዶ መንገዱ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በኩል የሚከናወነውን የትራፊክ መብራት ተከላ ሥራን ጨምሮ ሌሎች ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራዎች በአካባቢው በትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ በማያሳድር መልኩ በቀጣዮቹ ቀናት የሚከናወኑ ይሆናል።

በካርል አደባባይ ላይ የተከናወነው የትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ ሥራ በተያዘለት ዕቅድ መሰረት እንዲከናወን በትዕግስት ለጠበቃችሁ የመንገዱ ተጠቃሚዎችና ለባለድርሻ አካላት ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ምስጋናውን ያቀርባል።

በዚህ ስፍራ የመታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸው የነበረው ሚስተር ካርል ሄንዝ በም፣ ሀገራችን በተፈጥሮ አደጋ በተፈተነችበት ወቅት በሰብዓዊነት ያከናወኑት ሰናይ ተግባር ምንጊዜም በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲዘከር ይኖራል፡፡

በመሆኑም የክፉ ቀን ባለውለታችን የነበሩት የሚስተር ካርል ታሪክ ወደፊትም በትውልድ ሲዘከር እንዲኖር፣ በመንገድ ሥራው መክንያት የተነሳው ሐውልት በተመረጠ ሥፍራ ላይ መልሶ የሚቆም ከመሆኑም በተጨማሪ ከብስራተ ገብርኤል ወደ ልደታ ፍርድ ቤት የሚወስደው መንገድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል በስማቸው የሚሰየም ይሆናል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.