ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት 6 ወራት 360 ኪ.ሜ የሚሸፍን የጥገና ስራ አከናወነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2015 የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት 360 ኪ.ሜ ርቀት የሚሸፍኑ ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎችን አከናውኗል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያዩ የከተማዋ ማዕዘናት እያከናወናቸው ከሚገኙ ልዩ ልዩ የመንገድ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን፣ በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ መንገዶችን ጠግኗል።
ከእነዚህም ውስጥ 39 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 266.3 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳትና ጥገና፣ 18.68 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ፣ 4.36 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ስራ፣2.56 የእግረኛ መንገድ መከለያ አጥር እና 19.43 ኪ.ሜ የመንገድ ቀለም ስራ ይገኝበታል። ባለፉት 6 ወራት በጠቅላላው 360 ኪ.ሜ የሚሸፈን ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራዎች በማከናወን ከዕቅዱ በላይ ማሳካት ችሏል።
ከዚህ በተጨማሪም 7 ሺ 795 የመንገድ ዳር መብራት መስመር ጥገና እና አምፖል የመቀየር ስራዎች በግማሽ ዓመቱ ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity