ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለውን አመራር ያሳተፈ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መካሄዱን ቀጥሏል።
የአመራር ውህደት እና ቅንጅት በከተማዋ ለተመዘገቡ እመርታዎች መሰረት መሆኑ፤
ከማዕከል እስከ ወረዳ እና ቀጠና ያለው የፓርቲ እና መንግሥት አመራር በቁርጠኝነትና በትጋት በመስራታቸዉ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን፤
በተለይም በአመራሩ መካከል ያለው ጤናማ የውድድር መንፈስና የላቀ የስራ ተነሳሽነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን፤
በማህበራዊ ጉዳዮች በተለይም በትምህርት እና ጤና ዘርፎች ከፍተኛ ውጤቶች መኖራቸውን፤
ከኢኮኖሚ አኳያም በርካታ ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በመፍጠር የሴቶች እና ወጣቶች ተጠቃሚነትን በስፋት ማሳደግ መቻሉን
አምራቾችና ሸማቾችን በቀጥታ ማገናኘት የሚያስችሉ የገበያ ማዕከላትን በመገንባት አገልግሎት ውስጥ ማስገባት በመቻሉ የገበያ ትስስርን በማሳለጥ የህዝባችንን የኑሮ ጫና ማቅለል መቻሉ፤
ከፍተኛ የገቢ አሰባሰብ አቅም በመፍጠርና ከተሰበሰበዉ አጠቃላይ ገቢ 71 በመቶ ያህሉን ለዘላቂ ልማቶችና የድህነት ቅነሳ ተግባራት በማዋል የህዝባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉ፤
የኮሪደር ልማቱ የፈጠረው የከተማ ውበት ፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ፍሰት ፣ የማኑፋክቸሪግ ዘርፉ መነቃቃት ፣
የከተማዋን ሰላምና ደህንነት በመንግሥትና በህዝብ የተባበረ ክንድ እውን በማድረግ አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ ፣ ሰላማዊ እና ለጎብኚዎቿ ጭምር ምርጥ መዳረሻ መሆን መቻሏ፤
የከተማዉ ነዋሪ ከመቼውም ጊዜ በላቀ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የአካባቢ የልማት ስራዎችን በመስራት ይበልጥ ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱ ወዘተ… በግምገማ መድረኩ የተነሱ ዋነኛ የትኩረት ማዕከላት ሆነዉ ቀጥለዋል ።
