+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በእግረኞች መንገድ ላይ መኪና በመንዳት ደንብ ተላልፈው የተሰወሩ አሽከርካሪዎች 300 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንትናው እለት በቂርቆስ ክፋለ ከተማ ወረዳ 03 ወሎ ሰፈር አካባቢ በተሠራው የኮሪደር ልማት መሰረተ ልማት የእግረኞች መንገድ ላይ በተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ ተላልፈው የተሰወሩ አሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ፖሊሶች ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን አስታወቀ ።

ግለሰቦቹ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት ክትትል በማድረግ 3 አሽከርካሪዎች ከነ ተሽከርካሪአቸው በቁጥጥር ስር በማዋል እያንዳንዳቸው 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር )በድምሩ 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቀጣቱን ገልጸዋል ።

ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን፣ለህዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ በሀላፊነት እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።

ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣንጥሪውን አቅርበዋል።

Comments are closed.