በተሽከርካሪ ጎማ አያያዝና አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የቴክኒክ ስልጠና ተሰጠ
የስልጠናው ተሳታፊዎች የሆራይዘን አዲስ ጎማ ፋብሪካን የምርት ሂደት ጎብኝተዋል፡፡
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር ጋር በመተባበር ከመጋቢት 23 እስከ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለሚመለከታቸው የስራ ክፍል ሰራተኞች በአራት ዙር በተሽከርካሪ ጎማ አያያዝና አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረገ የቴክኒክ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰሎሞን አሰፋ፤ ፋብሪካው ከ53 ዓመት በፊት መመስረቱን አስታውሰው፤ ለተለያዩ ሞዴል ተሸከርካሪዎችና ለሀገሪቱ መልክዓ-ምድር ተስማሚ የሆኑ ተወዳዳሪ ምርቶችን በማምረት በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው የጎማ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በመሆኑ ለሀገር ኩራት ሆኗል ብለዋል፡፡
አቶ ሰሎሞን አያይዘውም፤ ድርጅቱ በቀን ከ2 እስከ 3 ሺህ የሚደርስ የቤት መኪና፤ የቀላል እና የከባድ ተሽከርካሪ፤ እንዲሁም የኢንዱስትሪ እና የእርሻ ማሽነሪዎች ጎማ በማምረት፣ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የጎማ ምርቶችን ከመተካት ባለፈ የውጭ ምንዛሬ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የጎማ ትክክለኛ አያያዝና አጠቃቀምን በአግባቡ ተረድቶ ተግባራዊ ማድረግ፣ የጎማ አገልግሎት እድሜን በማራዘም የተቋምን ብሎም የሀገር ሀብትን ከብክነት ለማዳን እገዛ ያለው በመሆኑ የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሥልጠናው ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ የበኩላቸውንው አዎንታዊ ሚና እንዲወጡ አቶ ሰሎሞን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ የተቋም ለውጥና ድጋፍ ሰጪ ዘርፍ ስታፍ አሲስታንት አቶ አብደላ ረዲ በበኩላቸው፤ የሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ 370 ለሚሆኑ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የቀላልና ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች፣ ለመካኒኮች፣ ለግዥ፣ ለእስቶር እና ለጎሚስታ ሰራተኞች በተሽከርካሪ ጎማ አያያዝና አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ሥልጠና በመስጠት ለውጤታማ የሃብት አጠቃቀም መጠናከር ላበረከተው አስተዋፅኦ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ ሥልጠናው በተሽከርካሪ ጎማ አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ እንዳሰፋላቸው ጠቁመው፤ ከሥልጠናው በጨበጡት ግንዛቤ በመታገዝ የተቋሙን ውጤታማ የሃብት አጠቃቀም አሰራር ለማሳደግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡
በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ፤ የስልጠናውን አጠቃላይ ወጪ በመሸፈን በአራት ዙር ስልጠናውን ለሰጠው ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማንፋክቸሪንግ አ.ማ የምስጋና የምስክር ወረቅት በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ተበርክቶለታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር (X) ፡- https://twitter.com/AbabaCity
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ
