+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

“ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፦ ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር” በሚል መሪ ቃል የተሰናዳው ህዝባዊ ውይይት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል።

የምክክር መድረኩን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ በጋራ የመሩት ሲሆን በውይይቱ ላይ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የከተማችን ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ለውይይቱ እንደ ሀገር አቀፍ የተዘጋጀውን መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት ዶክተር ግርማ አመንቴ ለሀገራችን ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና ራስን መቻል የዚህ ዘመን አርበኝነት ማረጋገጫ መሆኑን ተናግረዋል።

በውይይቱ ወቅት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳቦች ማብራሪያ የሰጡት አቶ አረጋ ከበደ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙት የልማት ስራዎች ሃገራችን ወደ ብልፅግና ለምታደርገው ጉዞ ጉልበት መሆናቸውን ጠቅሰው ለዚህ ጉዞ መሳካት ሁሉም ለሰላም፣ ለወንድማማችነትና ለአብሮነት ቅድሚያ በመስጠት የሀገራችን አንድነት እና ሉዓላዊነት በፅኑ መሰረት ላይ መገንባት አለብን ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የህብረተሰብ ክፍሎች በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘውን መሰረታዊ ለውጥ በዘላቂነት በማስቀጠል በምግብ ራስን ከመቻል አልፎ ሀገራችንን ወደ ብልፅግና ማማ የማድረስ ሀገራዊ ራዕይን እውን ለማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም በቁርጠኝነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል::

Comments are closed.