በተለያዩ አካባቢዎች እየተገነቡ የሚገኙ የአክሰስ እና የኮንዶሚኒየም የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው
የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እያስገነባቸው የሚገኙ የልማት ተነሽዎች የመኖሪያ ቤት አካባቢ የሚገኙ የመንገድ የግንባታ ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራ ይገኛል፡፡
የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች፤ በራስ ኃይል እና በሥራ ተቋራጮች እየተገነቡ የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የመስክ ምልከታ ከተደረገባቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል ፉሪ ሀና ፣ ጎሮ ሥላሴ፣ አያት ጣፎ፣ እና አያት ጨፌ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ይገኙበታል።
በተጨማሪም፤ ቦሌ አራብሳ፣ አያት 49 ፣ አራብሳ ኬላ፣ አቦ ጨፌ እና ቦሌ በሻሌ አካባቢዎች እየተገነቡ የሚገኙ የልማት ተነሺዎች አክሰስ መንገድ የመስክ ምልከታ ከተደረገባቸው ፕሮጀክቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ ፤ የህብረተሰቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበሩ የነዘህን የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚስችል የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጅነር ታምራት ታደሰ፤ የልማት ተነሺዎች በተሰጣቸው ቦታ ላይ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚያስችላቸውን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር፣ የመንገድ የአክሰስ መንገድ ግንባታውን በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የራስ ኃይል መንገድ ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጅነር ብስራት ሙሉጌታ በበኩላቸው፤ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራር በየጊዜው የሚያደርገው የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በግንባታ ሂደት ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ለመፍታትና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከት መሆኑን ገልፀዋል፡፡


Previous Post
Next Post
Users Today : 1
Users Last 7 days : 326
Users Last 30 days : 1181